Post has attachment
Video
Video
Animated Photo
Video
Video
2/7/17
8 Photos - View album

Post has shared content

Post has shared content
#ስምሽን ቢጠሩ የማትጠገቢ
~የመንገድ ስንቄ ነሽ
~ የነፍሴ መጋቢ
~ምስጋናሽ ይብዛልኝ።
~ወደቤቴ ግቢ
Photo

Post has shared content
እንኳን ለፃድቁ አባታችን #አቡነ #ተክለሃይማኖት አመታዊ ክብር በዓል በስላም በጤና አደረሳችሁ የፃዲቁ አባታችን አቡነ #ተክለሃይማኖት በፀሎት ልመናቸውና በምልጃቸው አይለዩን አሜንን በቃልኪዳናቸው ሀገራችንን ይጠብቁልን አሜንን አሜንን!
Photo

Post has shared content

Post has shared content

Post has shared content
#ነገ ፪፫ እንኳን ለሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን ///አደረሳችሁ አሜን፡፡ ሰማዕቱ ባለንበት ጽናትና ብርታቱን ያድለን። አሜን// አሜን //አሜን

~~ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፣ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።ሰው አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል?ወይስ ሰው ስለነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለዉና፣ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ስራው ያስከብረዋል ።//ማቴ. ፩፮:፪፭÷፪፯//

~~እኔን የሚወድ ቢኖር እራስን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ/መከራዬን ሳይሰለች /ዕለት ዕለት ይከተለኝ ።//ማቴ.፩፲:፫፰፥፬፪/ /
~~ስለ ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ ፣እንዲሁም የሚሰደዱ ብጹዓን ይጠግባሉና ፣መጽናናትንም ያገኛሉና •••••ጌታ በተራራ ስብከቱ ከተናገራቸው፣ካስተማራቸው፣የህይወት ምግብ የሆነ ቃሉ //ማቴ. ፭ ÷፩ - ፍጻሜ //

❤†❤†❤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ❤†❤†❤

❤†❤†❤ “እኔ የክርስቶስ ወታደር ጊዮርጊስ መጣሁባችሁ” ሲላቸው ደንግጠው ይሸሹ ነበር። ❤†❤†❤

❤†❤†❤ ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ፣ ብሩህ፣ ሐረገወይን፣ ፀሐይ ማለት ነው። ቶማስስ ዘልዳ እንዲለው ሀገሩ ልዳ ነው። አባቱ ዞሮንቶስ (እንስጣስዮስ) በልዳ መስፍንነት ተሹሞ ይኖር ነበር። እናቱ ትዎብስታ (አቅሌስያ) ትባላለች። ማርታ ድስያ የሚባሉ እህቶች ነበሩት።

❤†❤†❤ አስር አመት ሲሆነው አባቱ ሞቶ ሞቶ ሌላ መስፍን ተሾመ። ደግ ክርስታናዊ ነበርና ወስዶ እያስተማረ አሳደገው። እርሱም ፈረስ መጋለብ ቀስት መወርወር ለመደ። ጦር ሜዳ ወጥቶ ከጠላቶቹ መሀል ገብቶ “እኔ የክርስቶስ ወታደር ጊዮርጊስ መጣሁባችሁ” ሲላቸው ደንግጠው ይሸሹ ነበር።

❤†❤†❤ ጽኑ የእምነት አርበኛ በመኳንንቱ በሹማምንቱ በነገስታቱ ፊት የማይፈራ ድንቅ ወጣትም ነበር። ሃያ ሲሞላው መስፍኑ የ 15 ዓመት ቆንጆ ልጅ ነበረችውና እሷን ድሮለት ሀብቴን ወርሶ ይኑር ብሎ ድግስ ሲያስደግስ ዳስ ሲያስጥለ ጌታ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዚህ አላጨውምና የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ። እርሱም ሀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ሄደ። ቤሩት በኢያርኮ አቅራቢያ ያለች ሀገር ናት። በዚያ በቤሩት ሰዎች እግዚአብሔርን የማያውቁ ለዴጎን የተንበረከኩ ናቸው።

❤†❤†❤ ቤሩታዊቷንም የሹም ልጅ ለዚሁ ዘንዶ ግብር ሊገብሩለት ከግንድ ወስዶ አሰሩለት። ቅዱስ ጊዮርጊስም በዚያ ሲያልፍ የልጅቱን የጩኸት ድምጽ ሰማ። እሱም ምን ሆነሽ ነው? አላት። ለደራጎን ተሰጥቼ ነው አለችው። አምላካችሁ ወዴት አለ አላት ምግቡን ሊፈልግ ሄዷል አለችው። ይህን እያነጋገራት እያለ ደራጎኑ ምድሪቱን እያነዋወጠ መጣ። ሂድ ይበለሃል ስትለው፤ እኔማ ምን አለኝ ከኔ ጋር ያለው ግን ከሱ ይበልጣል አላት። ሊበላው ሲቀርብ ስመ እግዚአብሔር ጠርቶ ቢያማትብበት በላዩ ያደረው ሰይጣን እንደ ጉም ተኖ እንደትቢያ በኖ ጠፋ፤ ሃይሉም ደከመ። ቤሩታዊቷ አንገቷን በታሰረችበት ገመድ አስሮት እሷ እየጎተተች እሱ በፈረስ ሆኖ ከተማ ደረሰ። ሕዝቡን ሊያስፈጅ ነው ብለው ይሸሹ ጀመር። አጽናንቶ መለሳቸው። ንጉሱ ዱድያኖስ ግን ተነሳስቶበት ክርስቶስን ካድ ባለው ጊዜ አምላኬ ክርስቶስን አልክድም በማለቱ ተቆጥቶት ጥጋውን በመቃጥን አስተፍትፎታል፤ ረጅም ችንካሮች ያለበት የብረት ጫማ አጫምቶታል፤በችንካር አስቸንክሮታል፤ በፈላ ውሃ ውስጥ አስጨምሮታል።

❤†❤†❤ አጥንቱን አስከስክሶታል። መሄድ እስኪያቅተው ድረስ፤ መርዝም በጥብጦ አጠጥቶታል። በመንኩራኩር አስፈጭቶት ከጥልቅ ጉድጓድ ጥሎታል። ብዙውን ጊዜ በመንኩራኩር ተፈጭቷል፤ በኋላም በደብረ ይድራስ ላይ አጥንቱን በትኗል። መከራ ፈተና አብዝቶበታል። ፯ ጊዜ ሞቶ ፯ ጊዜ ተነስቷል።

❤†❤†❤ አቤት የቅዱሳን መከራቸ፤ ለዚህ እኮ ነው ቅዱስ ጳውሎስ
“እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና።❤†❤†❤ (ዕብ.፲፩፡፴፫-፵) 11፡33-40

❤†❤†❤ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።❤†❤†❤ (ማቴ.16፡25-27
❤†❤†❤ እኔን የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ /መከራዬን ሳይሰለች/ ዕለት ዕለት ይከተለኝ፡፡❤†❤†❤ ማቴ 10፡38-42 እንዲል ወንጌል
†❤† ስለ ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ፣ እንዲሁም የሚሰደዱ ብጹዓን ይጠግባሉና፣ መጽናናትንም ያገኛሉና… ጌታ በተራራ ስብከቱ ከተናገራቸው፣ ካስተማራቸው የሕይወት ምግብ የሆነ ቃሉ ማቴ.5፡1-ፍጻሜ

❤†❤†❤ ጊዮርጊስ ሆይ ጨካኝ ቁጡ በሆነው በዱድያኖስ አደባባይ ልዩ ልዩ ተዓምራትህን እንደማድረግህ በጠዋት በማታ በከንቱ ነገር የሚነሳሱብኝ ጠላቶቼ ሁሉ እንደ አመድ በነው እንደ ጢስ ተነው ይጥፉ፡፡

❤†❤†❤ ጊዮርጊ ሆይ ሰማዕታት ሁሉ አለቃ እንደመሆንህ ቀድሞ ሰብዓ ነገስታትን እንደደመሰስካቸው ነበልባላዊ በምትሆን ጸሎትህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፡፡
ተዓምረኛው ሰማዕት ሆይ ቀድሞ የቢፋሞንን ልጅ ከሰዕበተ ሃጢአት ሰውነቱን እንድቀደስከው መንግስተ ሰማያትን ለመውረስ እበቃ ዘንድ ሰውነቴን በፍጹም መቀደስ ከሃጢአት ርኩሰት ንጹህ አድርግልኝ፡፡
ተዓምረኛው ሰማዕት ሆይ ሙታንን የማስነሳት ሥልጣን ተሰጥቶሃልና አቤቱ ቤሩታዊትን ከአፈ ዘንዶ እንዳዳንካት እኔን ከእለተ እኪት ከዘመነ መንሱት በጸሎትህ አድነኝ፡፡


❤†❤†❤ አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ማረን፤አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ራራልን፤ አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ይቅር በለን፡
እግዚአብሔር አምላካችን ሰማዕታትን በደም ቅዱሳንን በገዳም ሐዋርያትን በአጽናፍ ዓለም መላዕክትን በአጽራርያም እንዳጸናቸው እኛ ሁላችንንም በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን በቅድስት ቤተክርስቲያን በበጎ ምግባር በጾም በጸሎትና በትሩፋት ያጽናን አሜን//// አሜን//// አሜን!!!
Photo

Post has shared content
#እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የተናገረውን ነገር (መዝሙር 44፡14 ጀምሮ ያለውን) ‹‹ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር›› ‹‹ገጸ ምሕረትሽን፣ ገጸ ረድኤትሽን ለማግኘት፤ አንድም በቁሙ(በቀጥታ በጥሬ ትርጉሙ) በዚህ ዓለም የከበሩ የገነኑ ህዝቦች ሁሉ ፊትሽን ለማየት ይለምናሉ፡፡

~፩፤ልቤ፡መልካም፡ነገርን፡አፈለቀ፥እኔ፡ሥራዬን፡ለንጉሥ፡እነግራለኹ፤አንደበቴ፡እንደ፡ፈጣን፡ጸሓፊ፡ብርዕ፡ነው።
~፪፤ውበትኽ፡ከሰው፡ልጆች፡ይልቅ፡ያምራል፤ሞገስ፡በከንፈሮችኽ፡ፈሰሰ፤ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡ባረከኽ።
~፫፤ኀያል፡ሆይ፥በቍንዥናኽና፡በውበትኽ፡ሰይፍኽን፡በወገብኽ፡ታጠቅ።
~፬፤ስለ፡ቅንነትና፡ስለ፡የዋህነት፡ስለ፡ጽድቅም፡አቅና፡ተከናወን፡ንገሥም፤ቀኝኽም፡በክብር፡ይመራኻል።
~፭፤ኀያል፡ሆይ፥ፍላጻዎችኽ፡የተሳሉ፡ናቸው፥እነርሱም፡በንጉሥ፡ጠላቶች፡ልብ፡ውስጥ፡ይገባሉ፥አሕዛብም፡በበታችኽ፡
ይወድቃሉ።
~፮፤አምላክ፡ሆይ፥ዙፋንኽ፡ለዘለዓለም፡ነው፤የመንግሥትኽ፡በትር፡የቅንነት፡በትር፡ነው።
~፯፤ጽድቅን፡ወደድኽ፡ዐመፃንም፡ጠላኽ፤ስለዚህ፥ከባልንጀራዎችኽ፡ይልቅ፡እግዚአብሔር፡አምላክ፡የደስታ፡ዘይትን፡ቀባኽ።
~፰፤በልብሶችኽ፡ዅሉ፡ከርቤና፡ሽቱ፡ዝባድም፡አሉ፤ከዝኆን፡ጥርሶች፡አዳራሽ፡ደስ፡ያሠኙኻል።
~፱፤የንጉሦች፡ሴት፡ልጆች፡ለክብርኽ፡ናቸው፤በወርቅ፡ልብስ፡ተጐናጽፋና፡ተሸፋፍና፡ንግሥቲቱ፡በቀኝኽ፡ትቆማለ ች።
~፩፲፤ልጄ፡ሆይ፥ስሚ፡እዪ፡ዦሮሽንም፡አዘንብዪ፤ወገንሽን፡ያባትሽንም፡ቤት፡ርሺ፤
~፩፩፤ንጉሥ፡ውበትሽን፡ወዷ፟ልና፥ርሱ፡ጌታሽ፡ነውና።
~፩፪፤የጢሮስ፡ሴቶች፡ልጆች፡እጅ፡መንሻን፡ይዘው፡ይሰግዱለታል።የምድር፡ባለጠጋዎች፡አሕዛብ፡በፊትኽ፡ይማለላ ሉ።
~፩፫፤ለሐሴቦን፡ንጉሥ፡ልጅ፡ዅሉ፡ክብሯ፡ነው፤ልብሷ፡የወርቅ፡መጐናጸፊያ፡ነው።
~፩፬፤በዃላዋ፡ደናግሉን፡ለንጉሥ፡ይወስዳሉ፥ባልንጀራዎቿንም፡ወዳንተ፡ያቀርባሉ፤
#የሕይወት መብልና መጠጥ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለማግኘት ማደሪያ ትሆነው ዘንድ የመረጣትን ድንግል ማርያምን ማክበርና ማመስገን ይገባል፡፡ አምላካችን ድንግል ማርያምን የምናመሰግንበት መልካሙን አንደበት ክብሯን የምናይበት ውሳጣዊ ዓይነ ኅሊና ያድለን፡፡ አሜን///አሜን ///አሜን

💒ስላም ለኪ እያለ 💒
ሰላም ለኪ እያለ
ሀርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምፅ ተስማ
ተሰማ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ

ውሃ ስትቀጂ ክንፉን እያማታ
ሊያበስርሽ የመጣው በታለቅ ደስታ
ከሞገስሽ ብዛት ከሞገስሽ ብዛት ሲታጠቅ ሲፈታ
አቅርቦልሽ ነበር የክብር ሰላምታ

አዝማች……………………………

የምሥራቹን ቃል ሚስጥር ተሸክሞ
ገብርኤል ተላከ ሊያረጋጋት ደሞ
እርጋታ ተሞልታ እርጋታ ተሞልታ ነገሩን መርምራ
የመላኩን ብስራት ሰማችው በተራ

አዝማች……………………………

ይደሰታል እንጂ መንፈሴ በአምላኬ
በምስጋና ሳድር ዘወትር ተንበርክኬ
ሀሳቤ ለቅፅበት ሌላ መች ያስባል
ለኔ ልጅን መውለድ እንዴት ያቻለኛል

አዝማች……………………………

ካንቺ የሚወለደው ንዑድ ነው ክቡር
የተመሰገነ በሰማይ በምድር
ሚስጥሩ ሃያል ነው ይረቃል ይሰፋል
ካንቺ በቀር ይህን ማን ይሸከመዋል

አዝማች……………………………

እፁብ ነው ድንቅ ነው አንቺን የፈጠረ
አንቺን በመውደዱ ሰውን አከበረ
አለም ይባረካል አለም ይባረካል በማህፀንሽ ፍሬ
ክብርሽን አልዘልቅም ዘርዝሬ 
Photo

Post has shared content
አሜን አሜን አሜን ዝማሬ መላእክትን ያስማልን
እልልልልልልልልልልልል 👏 👏 👏 👏 👏 👏 👏 👏 👏 👏 👏 👏 👏 👏 👏 👏

Post has shared content
Wait while more posts are being loaded