Post is pinned.
ሀበሻ ፍቅር ናት
እውነት & ሀስት

Post has shared content
#ፍቅር_ያዘኝ_እንዴ
ጨርቃ ስትወጣ ከጎኔ ቁጭ ብለህ
በአይኔ አይሀለሁ
ከዋክብት ሲጓዙ ከነሱ መካከል እፈልግሀለሁ
ከፀሀይዋ ጋራ ብትወጣ ብዬ
ጠዋት በማለዳ እጠብቅሀለሁ
አንዳንደም በህልሜ አቅፊህ አድራለሁ
ዝም ብለህ ባሳቤ ትመላለሳለህ
ምክናቱን ባላውቅም ትናፍቀኛለህ
ያነጫንጨኛል ላገኝህ እሻለሁ
በሰበብ ባስባቡ ስላንተ አወራለሁ
የፀድቄ ሽልማት የኔ ገነት ውዴ
አረ ጉድ ፈላብኝ ፍ_ቅ_ር ያዘኝ እንዴ ??
ሰምተሀል eko
Photo

Post has shared content
ማንበብ የሚችል ሁሉ ያንብበው!
በቀን 3 ግዜ ትበላለህ?
* ገላህን መሸፈኛ ልብስ አለህ?
* ቀን ደክሞህ ውለህ ማታ ምታርፍበት ጎጆ አለህ?

-እንግዲያውስ እወቅ አንተ በአለም ላይ ካሉት ከ75% በላይ ሰዎች የተሻለ ኑሮ ላይ ነህ!!
* ኪስህ ውስጥ አንዳድንድ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ምትገዛበትና ምትፈልግበት ቦታ
ምትንቀሳቀስበት ገንዘብ ካለህ? ------ አንተ ከአለማችን 18% ሃብታሞች ውስጥ አንዱ ነህ!
* ይቺን ቅጽበት ያለምንም ህመም በሙሉ ጤንነት እያሳለፍክ ነው?*
--በዚች ሰአት በአለም ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በሞት አፋፍ ላይ ሆነው ከሚያጣጥሩና አልጋ ላይ ሆነው ከሚሰቃዩት ውስጥ አይደለህምና ትልቁ እድለኛ ነህ።
ይሄን መልእክት እያነበብክና እየተረዳኸው ነው?
ልብ በል በአለም ላይ ከ3 ቢሊዮን በላይ ማየት ማንበብ ማይችሉ እንዲሁም የአይምሮ ህመምቶኞች ይህን ማድረግ አይችሉምና ከነሱ ውስጥ አንዱ ባለመሆንህ ትልቁ እድለኛ ነህ !!!
ስለሌለህ ነገር እያሰብክ ከማዘን ይልቅ ቆጥረህ በማጨርሰው የፈጣሪህ ስጦታ ደስተኛ ስትሆን ህይወትህ የበለጠ ቀላል ይሆናል!!
ሁሌም ፈጣሪን እናመስግነው።በኔበኩል ተመስገን ፈጣሪ!
ካነበብኩት።
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።

Photo

Post has attachment
????
Photo

Post has shared content
" የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ"

ድሮ ነበር... አንድ በጊዜና በጥረቱ ብዛት ከድህነቱ ተላቅቆ ባለፀጋ የሆነ ሰው ነበረ። ቤቱ ውስጥ በአሽከርነት እንድታገለግለው ከገጠር ያመጡለትን ሴት ገና ሲያያት ይደነግጣል። በወቅቱ ሴቲቱ የለበሰችው አዳፋ ልብስ ነበር። እሱም በዝቶ ገላዋ ላይ ተበጫጭቋል። ለእግሯም ባዶ እግር ከመሆን የማይሻል የተበጣጠሰ ላስቲክ ጫማ (ኮንጎ) ነበራት። ስትራመድ እየጎተተችው፣ ጣቶቿም ወጣ ገባ ይሉ ነበር። እየሮጠች ያስጎነጎነችው የሚመስለው ፀጉሯም ተክበስብሶና አዋራ ተሰግስጎበት ለዓይን አይማርክም። ከጉዞ ብዛት ፊቷን ያወረዛው ላብም ውበቷ ላይ አጥልቶባት ይጨንቃል።

እድሏ ሆኖ ግን በዚህ ሁሉ መሀል የአዲሱ ጌታዋን ልብ ማቅለጥ አልተሳናትም ነበር። ነፍሱ እስክትበር ደንግጦ ነበር የተመለከታት። ባለፀጋው ከሀብቱ ብዛትና ከኑሮው ጥራት የተነሳ ቤቱ የሚቀጠሩ አገልጋዮችን ልብስ በአዲስ እንዲቀየር ትዕዛዝ ያስተላልፍ ነበርና፥ እንደ ልማዱ ያን ቀንም በአስቸኳይ እንዲፈፅሙ ለነባር አገልጋዮቹ ትዕዛዝ አስተላለፈ።

ሴቲቱ ልብሷ በአዲስ ተተካላት። ታጥባም ፀጉሯን በአዲስ ተጎነጎነች። ውበቷም በአዲስ እንደተሰራ ሁሉ ሽልቅቅ ብሎ ወጣ። …ደስም አለው። አፈቀራት ። አዲስ ለባብሳ ገና እንደተመለከታት "ኦ የማስባት ሴት.... እስከዛሬ ድረስ የጠበቅኋት የጎን አጥንቴ..." ሲል ለራሱ አጉተምትሞ፥ እርሷ ሳትሰማ ሌሎች አሽከሮቹን (ነባሮቹን) ቅያሪ ልብሶቿን እንዲያመጡለት ጠየቀ።

እነሱም "እንዴ ጌታችን እንዴት ይሆናል? ልብሶቹ ከመነተባቸው ከማደፋቸው የተነሳ ያዩዋቸው ዘንድ አይመጥኑዎትም! ስለምን ፈለጉዋቸው?" ብለው ቢያቅማሙ ገስፆ ላካቸው።

ከዚያም ብር ብለው ወጥተው ብር ብለው አመጡለት። ድሪቶዋን። እርሱም ተቀብሎ አሰናበታቸው። ምንጉድ እንደሆነ ለማጣራት ቢጓጉም የጌታ ትዕዛዝ ነውና ካለ ልባቸው በሽቅድምድም ወጡ።

ካለወትሮው ቤቱን ሲያስጎበኛትና የስራ ድርሻዋን ሲያስረዳት ቆይቶ፣ መኝታ ክፍሉ ደረሱና እዚያ ያለ ያማረ ሳጥን እየጠቆማት የስራ ጉዳዮችን የተመለከቱ ነገሮች ስላሉት ከቦታው እንዳታንቀሳቅሰው።.እርሷም ታማኝ፤ ከዚያ ወዲያ ጭራሽ ሳጥኑን ለዓይኗም ረስታዋለች። (መቼስ የዛሬ ብትሆን እንዳትነካው ‘ንኪው’ ማለት ነበር።)
እናም ሲኖሩ ሲኖሩ... ስሜቱን መቋቋም አቃተው። በትህትናም ሚስቱ እንድትሆን እንደመረጣትና እንደሚያፈቅራት ዘከዘከላት። ደስም አላት። ብቻ የሚቀልድባትም መስሏት ነው መሰል ተሽኮረመመች።

"ኧረ እንዴት ይሆናል?" ስትል እያልጎመጎመች! በልቧ.... ባንዳፍ! የኔ ንጉስ! የኔ ጌታ! ኧረ እንዴት ተባርኬያለሁ አያ?!’ ስትል... ደግሞ አፍ አውጥታ ኧረ አትቀልድ አንተው! ብላ ጌታዋን ልትሳፈጥ እየዳዳት.... ብቻ ምንስ ብትሆን ያው ሴት ነችና ወግ የባህሉን ተግደርድራ እሺ አለች ። ተግባቡ፣ ተዋደዱ። በነገር ሁሉም ‘አንተ ትብስ አንቺ’ ተባብለው ሊኖሩ፤ እግዚአብሔር ልጆች ቢሰጣቸው ደግሞ ምድርን ሊሞሏት.... ተስማሙ። አሳዳሪዋ ባለቤቷ ሊሆን ነውና ሽማግሌ ላኪም ተቀባይም ሆኖ ጉድ ተባለላቸው። ለሰሪና ላሰሪው። ድል ባለ የባለፀጋ ድግስ ተዳሩ። ላልከዳሽ፣ ላትከጂኝ ተባብለው። በወግ በማእረግ ቃል ተገባቡ።

ሲኖሩ ሲኖሩ... ልጆች ተወልደው፣ ቤቱ ውስጥ ተድላ ፀጋው ከነበረው በላይ በዝቶ፣ እንግዶች የሚያርፉበት - የዓለም የሲሳይ የሚባል ቤት ሆነ። እርሷ ግን የመጣችበትን ስትረሳው ብዙም አልቆየ። ወዲያው ከንጉስ ቤት አኗኗር ጋር ራሷን አጣጥማና አስማምታ መኖር ጀመረች። ቋንቋውን፣ ስርዓቱን፣ ባህሉን፣ ዘመዱን፣ ቀዳዳውን፣ ድፍኑን... ሁሉን በአጭር ጊዜ አበጥራ አወቀች። አውቃም ልቧ አበጠ። መዝለል፣ ውጭ ውጭ ማለት አማራት።
ባል ነገሩን ሁሉ እየተመለከተ ይታዘባል። በዘዴ ፀባይዋን ታርም ዘንድ ሸንቆጥ ያረጋታል። እሷ እቴ... መስሚያዋ ጥጥ ሆኖባት ነበር። ጭራሽ ከአንዴም ሁለቴ ከሌሎች ሰዎች ጋር መሄዷን ይሰማል። በሰማበት ቅፅበት እሳት ይለብስ፣ ይጎርስና ወዲያው ደግሞ መለስ ይላል። ከልቡ ሳይቀዘቅዝ እንደበረደለት፣ ምንም እንዳልተፈጠረበት ሰው - ዝም ጭጭ። ድራማውን መስራት።.... የሆዱን በሆዱ አድርጎ
"እንዴት ዋልሽልኝ እመቤቴ?" ይላታል።

መልሷም ስርዓት ያጣ ጀመር። ምሬቱ ሲደራረብ ለቅርብ ጓደኞቹ፣ ከዚያም ለቅርብ ጓደኞቿ ከዚያ ደግሞ ለተከበሩ ሽማግሌዎች ተናገረ። ይመክሩ ይዘክሩለት ዘንድ ጠየቀ፤ አሳሰበ። ነገሩ መላ ቅጡን ማጣቱን የተረዱት ሰዎች ሁለቱንም ቀን ቆርጠው ሰበሰቧቸው።

ከዚያም ሁለቱም አሉ ያሉትን ችግር እንዲናገሩ እድል ሲሰጣቸው፣ እርሱ እንደሚወዳትና ፀባይዋን አስተካክላ ... እግዚአብሄር እስከፈቀደላቸው ጊዜ ድረስ ከርሷ ጋር አርጅቶ በተድላና በደስታ መኖር እንደሚፈልግ ተናገረ።

እርሷም በባልነት ምንም እንዳልበደላት ገልፃ በትዳር ታስሮ ቤት መዋሉ ስለመረራት ንብረት ተካፍላ ልጆቿን ማሳደግ እንደምትፈልግ ተናገረች። ሁሉም ተገረመ።

ባሏም ሽማግሌዎቹም በመልሷ ተገረሙ ። (እርሷ ግን ምናልባት መገረማቸው እንዳስገረማት እንጃ....) ሽማግሌዎቹ ለዳኝነት ተቸግረው እየተቅበዘበዙ..... አንዴ ባልን አንዴ ሚስትን ቀና ብለው "በእንዴት እናድርገው" እየተመለከቱ ቆዩ።

እርሱም ነገራቸው ገብቶት ኖሮ "ፈቃዷ ይሁን" ሲል መለሰላቸው። “ንብረት ከመከፋፈላችን በፊት ግን እስከዛሬ ስለነበራት መልካምነት አንድ ስጦታ አለኝ።” ሲል ተናገረ።

እነሱም በትህትናውና በመረጋጋቱ ተገረሙ። እርሷም ግራ ገባት። "ምን ይሆን?" ብለው በጉጉት ጠበቁ።

እርሱም .. “እመቤቴ ሂጂና ከመኝታ ክፍል ስትመጪ አትንኪው ያልኩሽን ሳጥን አምጪው አላት።”

እርሷም የመጣችበትን ጊዜና ቦታ ዘንግታዋለችና “ከየት ስመጣ?” አለችው።

እርሱም “ከገጠር ” አላት።

እርሷም .....የረሳችው ነገር ስለተቆሰቆሰባት ተናዳ እየተመናቀረች ከመኝታ ቤት ሳጥኑን ይዛው መጣች። ፓ! ያማረ ነበር። በወርቅ ቅብ የተለበጠ ሳጥን። ልቧ እንደ አታሞ ድም ድም ይል ያዘ። ምን የሷ ብቻ? የሽማግሌዎቹም

ከዚያም ቁልፉን ሰጥቷት ከፍታው ውስጥ ያለውን እንድትወስድ ነገራት።..... አክሎም “ምናልባት የጉዞሽን አቅጣጫ ትለዪና ትወሲኝ ዘንድ ይረዳሽ ይሆናልና ነገም በጥንቃቄ አስቀምጪው" አላት። ከፈተችው ስትመጣ የለበሰቻቸው ልብሶች ነበሩ። ቆራጣ ኮንጎዋም አለ። የተሸነጣጠቁ እግሮቿን በኮንጎው፤ ቆስቋላ ገላዋን በቡትቶዎቹ አየቻቸው። ሀዘኑ ፀፀቱ ደቆሳት፤ ከፋት፤ ግራ ገባት። ሽማግሌዎቹም ግራ ገባቸው ግራ ተጋቡ እግሩ ላይ ወድቃ አለቀሰች። ፤ስቅስቅ ብላ... በእድሏ፤ በሰራላት ስራ የት እንደነበረች በመርሳቷ በጥጋቧ፤ በበደሏ በሁሉም ነገር ምርርርርር ብላ ምህረት ጠየቀች።
ከዚያም አብረው መኖር ቀጠሉ። ልብሶቹና ሳጥኑ ግን ቦታ ቦታቸው ተመለሱ።

የነገን ማን ያውቃል?
Photo

Post has attachment
Photo

Post has attachment
Photo

Post has attachment
እኔ B ነኝ
እናተስ???
Photo

Post has attachment
መልካም ቀን ይሁንላቹሁ
Photo

Post has attachment
Photo
Wait while more posts are being loaded