Post is pinned.Post has attachment
�አሸንዳ_እና_ዕርገትዋ ( ሃይማኖታዊ ወይስ ባህላዊ ? )

የእመቤታችን የዕርገትዋ በዓል ሲመጣ በሃገራችን በተለይም በሰሜኑ ክፍል የሚታይ አንድ ሃይማኖታዊ ክንዋኔ አለ:: አሸንዳ!! የአሸንዳ በዓል የሴቶች በዓል ሲሆን ከነሐሴ 16 ጀምሮ እንደየ አካባቢው እስከ 2ሳምንትም እስከ አዲስ ዓመትም ሊደርስ የሚችል ነው:: ይህ በዓል በብዙዎች ዘንድ ባህላዊ እንጂ ሃይማኖታዊ መሰረት እንዳለው ካለመታወቁ የተነሳ ለበዓሉ የሚሰጠውን ክብርና የአከባብረ ሁኔታ እንዲቀየር አድርጎታል:: አንዳንዶች ደግሞ በዓሉ "ከባህል የተወለደ ነው" ለማለት ታሪክን ለመምዘዝ ይሞክራሉ:: ነገር ግን የበዓሉን ታሪካዊ ዳራና የአከባበር ስርዓት ስናስተውል በዓሉ ሃይማኖታዊ ትሩፋት ይልቁንም ደግሞ የእመቤታችንን ዕርገት ይበልጥ የሚያስረዳ መሆኑን እንረዳለን:: ይህም...
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
1)ቀኑ የደናግል ሴቶች በዓል መሆኑ:-የአሸንዳ በዓል በተለያዩ አካባቢዎች የተለያየ የጊዜ ርዝማኔ ያለው ቢሆንም በሁሉም አካባቢዎች የሚጀመረው ነሐሴ 16 ነው:: ይሄም የእመቤታችን የዕርገትዋ በዓል ነው:: በዚህ ላይ በዓሉ የሴቶች ብቻ መሆኑ የሚነግረን ነገር አለ:: እመቤታችን ስታርግ 36ቱ ቅዱሳት አንስት ዳዊት በበገናው ሲዘምርላት፣ መላእክት ሲያከብሯት አይተው እነርሱም ሲያመሰግንዋት ታይተዋልና ነው:: በተለይም ደግሞ በአይሁድ ልማድ "በእናንተ (በሔዋን) ምክንያት ከገነት ወጣን" እያሉ ሴቶችን የኃጢአትና የመርገም ምሳሌ እንደሆኑና ዘራቸውንም ሲቆጥሩ በወንድ አባታቸው እንጂ በእናታቸው በኩል መቁጠር እንደ ነውር ይቆጥሩ ነበር:: ነገር ግን በሔዋን ምክንያት የሞት ፍሬ እንደበላን በድንግል ምክንያት የሕይወትን ፍሬ ክርስቶስን በልተናልና እመቤታችን በተለይም የሴቶች ትምክሕት ናት! ሔዋን ከሁሉም ቀድማ ጥንተ አብሶን ለማግኘት ቀዳሚ ብትሆንም ከሰው ወገን ደግሞ እመቤታችን ከጥንተ አብሶ ነፅታ ለመገኘት ቀዳሚት ናትና! አንድም የመርገም ምሳሌ ለነበሩት ሴቶች �#�የነፃነት_ምልክት� ናት! ይሄም የአሸንዳ በዓል "የሴቶች የነፃነት ቀን" መባሉ ይሄንን ክርስቲያናዊ መልዕክት ይበልጥ የሚያስረግጥልን ነው:: በዚህም ላይ በዓሉ የሴቶች ብቻ ሳይሆን �#�የደናግል_ሴቶች� በዓል ነው:: ይሄም የእመቤታችንን ድንግልና የሚያስታውስ ሲሆን አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው እንዳለው <ትምክሕቶሙም ለወራዙት ወደናግል ወመነኮሳት -- የወጣቶች የደናግልና የመነኮሳት መመክያ ናት> እንዳለው የድንግልናቸውን ዋጋ የምታሰጣቸው ናትና ደናግል ያመሰግኗታል ይዘምሩላታል::
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
2)የአለባበስ ስርዓቶቹ:- ሴቶቹ ለበዓሉ መስቀል ያለበት አዲስ ቀሚስ፣ በአንገት የሚደረግ የብር/ብረት መስቀልና በተለይም ደግሞ በወገባቸው የሚታጠቁት የአሸንዳ ቅጠል ነው:: የመስቀል ሐብልና በመስቀል ያጌጠው ቀሚስ ክርስቶስን የሚሰብኩበትና በዓሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን የሚመሰክሩበት ሲሆን፣ የአሸንዳው ቅጠል ደግሞ የኖህ ርግብ "ሰላም ሆነ" ስትል ቅጠል ይዛ ተገኝታለችና እመቤታችንም "መርገም ቀርቶ ሰላም ሆነ" ስትል ክርስቶስን ይዛ ተገኝታለችና ነው! በዚህም እመቤታችን የሰላም ምልክት መሆንዋን የሚናገሩበት ነው:: አንድም ቅጠሉ የመላእክት ምሳሌ ነው:: እርስ በርሱ መታሰሩ ደግሞ እመቤታችን ስታርግ መላእክት ክንፍ ለክንፍ ተያይዘው <ነያ እህትነ - እንሆ እህታችን> እያሉ እንዳመሰግንዋት የሚያመሰጥር ነው::
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
3)ከቤ/ክ መጀመሩ:- ደናግሎቹ ለበዓሉ ከተሰበሰቡ በኋላ አስቀድመው በ16 ቀን ጠዋት ወደ ቤ/ክ በመሄድ ጸሎት አድርሰው፣ እግዚአብሔርንና እመቤታችንን ያመስግናሉ:: ከዚህም በቤ/ክኑ የእመቤታችንን ዕርገት ከታወጀ ብኋላ አስቀድመው ወደ ደብሩ አስተዳዳሪ ሄደው፣ ተባርከው፣ ከዚያም ይሄንን የድንግልን ዕርገት ለሰው ሁሉ ያበስሩና እንኳን አደረሳችሁ ይሉ ዘንድ ተመርቀው ይሄዳሉ:: በየመንገዱና በየቤቱም እየሄዱ ዕርገትዋን የሚያሳዩ መዝሙሮችን ያቀርባሉ:: በሄዱበት ቤት፣ ሰው እንኳን ባያገኙ "የአሸንዳ ቅጠል" ከበሩ አስረው ይሄዳሉ! እንኳን አደረሳችሁ ለማለት!! ሰዎች ካሉም የቻሉትን ያህል ስጦታ ለደናግሎቹ ይሰጣሉ! በዚህም በዓል የተሰበሰበው ስጦታ ወደ ቤ/ክ ሄደው ያስረክቡታል እንጂ ለራሳቸው አይካፈሉትም! ስጦታው �#�የማርያም� ነውና!!
፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አሁን አሁን ግን ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው ይሄ ድንቅ በዓል ከጊዜ ብዛት የተንሳም ይሁን የሚከታተለው ሰው ባለመኖሩ፣ በዓሉን ከማይገልፁ ባህላዊ ክንዋኔዎች ጋር ተደባልቆ፣ ዕርገትዋን የሚያመለክቱ ግጥሞችና ዝማሬዎችም ጠፍተውና ወደ ዘፈን ተቀይሯል፣ በዓሉም የእመቤታችንን የዕርገትዋን ዜና የማብሰር ቀን መሆን ሲገባው ገንዘብ ወደ መለመን እየተለወጠና ከደናግሎቹም መሃል በዓሉ የእመቤታችን ዕርገት መሆኑ እንኳን የማያውቁበት ደረጃ ላይ ደርሰናል:: ስለዚህም በተለይም ይሄ �#�የአሸንዳ_በዓል� በድምቀት የሚከናወንባቸው አካባቢዎች ያሉ የባህልና የቱሪዝም ኤጀንሲዎች ይሄንን ሃይማኖታዊ በዓል ልክ እንደ ጥምቀትና የመስቀል ደመራ መሰረቱን ሳይለቅ ይከበር ዘንድ የበኩሉን አስተዋፅኦ ያደርግ ዘንድ አደራ እንላለን!
Video
Photo
8/16/18
2 Photos - View album

Post has attachment

Post has attachment
ደብረ ታቦር ወይንም ቡሄ! በመላው ሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበር በዓል ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዓቢይ (ዋና) በዓላት አንዱ ይሄ 'ደብረ ታቦር' የምትለው የቡሄ በዓል ነው።

⤵{የበዓሉ መሠረት}⤵
የዚህ በዓል መሠረት የክርስቲያን እምነት ሲሆን፣ ደብረ ታቦር በግዕዝ የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጥኤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደፀሐይ የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።

የማቴዎስ ወንገል ምዕራፍ ፲፯፦ ቁጥር ፩ እስከ ፭ " ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።"

ዓቢይ መሠረቱ ይሄ ሲሆን፣ በአገራችን የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት 'ቡሄ' የሚለውን ስያሜ አገኘች። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡

በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ (ሲያኖጉ) ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጡ፡፡ ታዲያ ያንን ማስታወሻ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የምናከብረውም ከዚህ በመነሣት ነው፡፡

Post has attachment

Post has attachment
☩☩☩💒 አይናችን ነሽ መርያም💒☩☩☩
አይናችን ነሽ ማርያም አንችን አይኩብ የተዋህዶ ልጆች እንወድሻለን ግቢ ከቤታችን በረክታችን ነሽ በሀሴት ቁመናል ደስታን ሰለወለድሽ የቀደመው እባብ እጂግ ተበሳጨ ባሸዋላይ ቆሞ መርዙን እየረጨ ከልጂሽ ምስክር ሊያስቀር ከዘሮችሽ እጂጉን ይተጋል ሊለየን ከጉያሽ ገብተሻል ላትወጭ አንዴ ከልባችን ጌታን ያየንብሽ ስለሆንሽ አይናችን የራቀው ቀርቦልን የረቀቀው ጎልቶ ያየነው ባንች ነው የጠፋው ተገኝቶ ወይኑን ያፈራሽው የወይን ሀረግ ድንግል ምግብን የሰጨሽን በቀራንዮ መስቀል ምልክታችን ነሽ የኛ መታወቂያ የምንተርፍብሽ ከጥፋት ገበያ የህይወት መገኛ የደስታ መፍሰሻ ፀዋሪተ ፍሬ የሀዘናችን መርሻ ግቢ ከቤታችን በረከታችን ነሽ የጎደለው ሁሉ ይሞላል በምልጃሽ ከሀገር ብንርቅ ከልፍኝ ከጓዳችን ስንቅ ነሽ ለመንገድ ምርኩዝ ለጉዟችን ባደርንበት አድረሽ በሄድንበት ሂጂ ለፃድቃል አይደለም ለሀጢያን አማልጂ

Post has attachment

Post has attachment
በይ እንግዲህ ቻይው
ልማድሽ ነው ጎንደር
ከሀገር በላይ ወልዶ
ከሀገር በላይ መቅበር
😢😢😢😢😢😢
Photo

Post has attachment
“ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኃበ እግዚአብሔር፤
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። መዝ67፤31

"ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን" - "ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ'

ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ሊቀ ጳጳስ በረከታቸው ይደረብን ለቤተክርስቲያን አንድነት የሚሞቱ ታላቅ አባት ናቸው

ዛሬም በሁለቱ ሲኖዶስ መታረቅ ለቤተክርስቲያን ታላቅ ደስታ እንደሚሆን ብፁዕ አባታችንም ቃለ ወንጌሉን እያነበቡ እንባቸው ይወርድ ነበር
Photo

Post has attachment
እጅግ ደስ የሚል ዜና!
ዋሽንግተን ዲሲ የምትገኘው የርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ወደ ኢትዮጵያው/ሃገር ቤት ሲኖዶስ መቀላቀሏን በይፋ አውጃለች

Post has attachment
ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ማለት ልዩ ነው ትርጉሙ።
➊.ኢትዮጵያ ማለት “ለአምላክ የሚሰጥ የወርቅ ሥጦታ” ማለት ነው።
:
➋.ኢት=አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ማለት ሲሆን ዮጵ= ቢጫ ወርቅ፣ ውድ ወርቅ፣ ልዩ ወርቅ ማለት ነው።
:
➌.ኢትዮጵያ ማለት እኔና እናንተ በምናውቃት ልክ ብቻ ያለች ሀገር አይደለችም።
:
➍.ኢትዮጵያ ማለት ከምድር ሀገራት ሁሉ እጅግ ምስጢራዊና ረቂቅ ሀገር ናት።
:
፩."ብሉይ ኪዳን!"
:
➊ኛ).ሊቀ ነብያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ ያስተማረው ኢትዮጵያዊው ዮቶር ነው።
:
ስለዚህ ለእስራኤል ከፈርዖን ነጻ መውጣት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና አለበት ማለት ነው።
:
አዎ የዮቶር ርስት ውብ ሀገር ኢትዮጵያ ነች።
:
➋ኛ).አሁንም የሊቀ ነብያት ሙሴ ሚስት ሲጳራ ኢትዮጵያዊት ነች።
:
ሲጳራ የኢትዮጵያዊው የዮቶር ልጅ ነች። ሙሴ ይቺን ሐበሻዊት ሴት በማግባቱ ወንድሙ አሮንና እህቱ ማርያም ያጉረመርሙበት ነበር። እግዚአብሔርም ገሰፃቸው።
:
➌ኛ).አብርሐምን የቀባው የክርስቶስ ምሳሌ የሚባለው የመጀመሪያው ካህን መልከጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነው።

ይህ ካህን በክርስትና አስተምህሮ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ተደርጎ ይቆጠራል።

➍ኛ).በሀገረ እስራኤል የራሷ ቦታ ያላት (ዴር ሡልጣን) ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች።
:
ይሄንን ቦታ ምዕራባዊያንና አንዳንድ የምስራቅ ሀገራት ለመውሰድ ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ታሪክ ይዘክራል።
:
➎ኛ).ከባቢሎን ዘመን አስቀድሞ የነበረው ብቸኛው የሰው ልጅ ቋንቋ (ግዕዝ) የሚገኘው ኢትዮጵያ /ቤተ-ክርስትያን/ ውስጥ ነው።

ይሄን ቋንቋ እኛ የቋንቋው ባለቤቶች ብናቃልለውም ቅሉ ዓለም ግን እጅግ የሚያከብረው ትልቅና ቀዳሚ ልሣን ነው። ይሄንን ደግሞ ራሳቸው ምዕራባዊያን ይመሰክራሉ። በዚህ ቋንቋ ብዙ እልፍ ድርሳናትና ምስጢራት ተከትበዋል።

➏ኛ).ጻዲቁ አባታችን የሄኖክ የልጅ ልጅ ኖኅ የተቀበረው ኢትዮጵያ/ጎንደር/ ውስጥ ነው።
:
የሰው ልጅ ከሰማይ ከተጣሉት መላዕክት (ኔፍሊሞች) በተማረው ምድራዊ ጥበብ ምክንያት ልቦናው ከፈጣሪው ራቀ።
:
ለምሳሌ ኮኮብ ቆጠራ፣ በአንገት የሚታሰሩ በጆሮ የሚንጠለጠሉ በእጅና እግር ጣቶች የሚታሰሩ ከንፈርንና ገላን የሚቀቡ ሁሉም ምድራዊ ጌጣጌቶች የመጡት ከወደቁት መላዕክት ወይም ከኔፍሊሞች ነው።
:
እነዚህ መላዕክት የሰውን ልጅ ከፈጣሪው እንዲርቅ ዝሙትን፣ መዳራትን፣ ያለ አግባብ መብላትና መጠጣትን አስተማሩት። በዚህም ምክንያት የሰው ልጅ ኅልቆ መሳፍርት ሀጢያትን በመስራቱ እግዚአብሔር ምድርን በንፍር ውኃ መላት፣ ሁሉም አለቁ፣ ኖኅና ቤተሰቦቹ ብቻ ቀሩ። ይህ ሰው መቃብሩ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
:
➐ኛ). ኖኅ ራሱንና ልጆቹን ከንፍር ውኃ ያዳነባት መርከቡን ያሳረፋት ኢትዮጵያ/ ጣና አካባቢ ከሚገኘው አራራት ተራራ ላይ ነው።
:
➑ኛ).የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረው ከአራት ባህሪያተ ስጋ ነው።
:
ከእነዚህም መካከል ደግሞ የተፈጠረበት እሳት ውኃና ነፋስ የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው። ከዚህም በመነሳት አንዳንዶች አዳምና ሄዋን ኢትዮጵያዊያን ናቸው ይላሉ።
:
እውነት ነው! ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ነች። ያች በቁፋሮ የተገኘች የዝንጀሮ አጽም ድንቅነሽ (ሉሲ) ስለተገኘችባት ሳይሆን የእግዜር የእጁ ሥራ የሆነው አዳም ስለተገኘባት ነው።
:
➒ኛ).ከገነት ከሚመነጩና ገነትን ከሚያጠጡ አራት አፍላጋት/ምንጮች/ ትልቁ ግዮን ኢትዮጵያዊ ነው።
:
ግዮን ከገነት ይመነጭና ወደ ምድር ይፈሳል፣ ከዚያም የኢትዮጵያን ምድር ይከባል። ይህ ወንዝ ጎጃም ውስጥ ሰከላ አካባቢ ግሽ ዓባይ የተሰኘ ቦታ ላይ ነው የሚፈልቀው። ከዚያም ሙሉ ጎጃምን እንደመቀነት ይዞርና ወደ ኔፍሊሞች መንደር ግብጽ ይፈሳል።
:
➓ኛ).ሞትን ሳይቀምስ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተወሰደውና አዕምሮውን መቶ በመቶ(100%) የተጠቀመበት ብቸኛው የምድራችን ሰው ሄኖክ ሐበሻ/ ኢትዮጵያዊ/ ነው።
:
እስከዛሬ ድረስ አዕምሮውን ሙሉ በሙሉ የተጠቀመ ምድራዊ ሰው የለም። የሰው ልጅ የአእምሮው ልዕልና የሚለካው በምድራዊ እውቀት ሳይሆን በሰማያዊ ጥበብ ነው።
:
ሰው የአዕምሮው ልዕልና (IQ) ሲያድግ ወደ ቅድስና ደረጃ ይሸጋገራል እንጅ ምዕራባዊያን እንደሚሉት በምድራዊ ጥበብና እውቀት አይመላም። ይሄን ደግሞ ያደረገ ብቸኛው ሰው ሐበሻው ሄኖክ ብቻ ነው።
:
➊➊ኛ).ሲዖልም ገነትም የሚገኙት በመላኩ 15 ክንድ ከምድር ከፍ ብለው ኢትዮጵያ (አፋር ኤርታሌ እና ጎጃም ጣና አካባቢ በቅደም ተከተል) ነው።
:
በድሮው ወሎ ክፍለ ሀገር በዛሬው አፋር ውስጥ የሚገኘው ኤርታሌ የሚባለው ቦታ የራሱ ሰማያዊ ምስጢር አለው።
:
እዚህ ቦታ ላይ የሚገኘው እሳተ ገሞራ ወይም የእሳት ባህር ሉሲፈር (ሳጥናኤል) የታሰረበት ቦታ መሆኑን አንዳንድ መዛግብት ላይ ለማንበብ ችያለሁ።
:
አዎ ይህ ቦታ የሲኦል መገኛ እንደሆነና ጎጃም የሚባለው ሀገር ላይ በተለይም ደግሞ ጣና ዙሪያ የገነት መገኛ ናቸው።
:
➊➋ኛ).በዓለም ትክክለኛነቱ የተረጋገጠለት የዘመን ስሌት ያለው ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ (ኢትዮጵያ) ውስጥ ነው።

ይህ የዘመን ስሌት አጽዋማትና በዓላት የሚከበሩበት ቀመር የቀናት ብሎም የዓመታት ስሌቱ ያልተበረዘና ትክክለኛ ነው።
:
➊➌ኛ).በነብያት እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የተባለች ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች።

አዎ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። መመኪያዋም አለኝታዋም እርሱ ነውና።
:
ይች ሀገር ከፈጣሪዋ ጋር ልዩ ትስስር ያላት የዓለማችን ብቸኛ ሀገር ነች። ፈጣሪ በስጋ የተመላለሰባት ሀገር እስራኤል እንኳን የኢትዮጵያን ያህል ክብር በፈጣሪ ዘንድ የላትም።
:
ለዚህ ደግሞ ማሳያ የሚሆነን ነገር አለ። እግዚአብሔር በነብያቱ በኩል እስራኤላዊያንን ሲገስጽ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያዊያን ልጆች (ሐበሾች) አይደላችሁም ነበር ያለ። ልብ በሉ! እንደ ኢትዮጵያዊያን!
:
➊➍ኛ).ታቦተ ጽዮን የሙሴ ጽላት የምትገኝባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች።
:
በአምላክ ትዕዛዝና ቀመር የተሰራችው ይህቺ ጽላት በጠቢቡ ሰለሞን የንግሥና ጊዜ የደቡብ ንግስት (ንግስተ አዜብ) ወይም የሳባ ንግስት (ንግስተ ሳባ) ተብላ በምትጠራዋ ንግስት ማክዳ ልጅ በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ነበር ወደ ሀገራችን የገባችው።
:
ምዕራባዊያን ይህቺን መመኪያችንን ጽላት ዘሙሴ ለመውሰድ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል። ነገር ግን አልተሳካላቸውም፣ አይሳካላቸውምም። ምክንያቱም እነርሱን ትታ በእኛ ምድር በሀገራችን ትኖር ዘንድ በእግዚአብሔር ፍቃድ መጥታለችና ሊወስዷት ቢኳትኑም አያገኟትም።

➊➎ኛ).ማንነቱን /መልኩን/ እንደነብር አይቀይርም የተባለ ጀግና ሕዝብ (የዛሬን አትመልከቱ ወደኋላ ተሻገሩ እንጅ) የሚኖርባት ምድር ኢትዮጵያ ነች።
:
አፍሪካዊያንን፣ ላቲኖችንም፣ ምዕራባዊያንንም ተመልከቱ፦ ሁሉም ማንነታቸውን ቀይረዋል፣ ሰው ከመሆን እየዎጡ ነው፣ ከፈጣሪ ርቀዋል።
:
አንዳንዶቻችሁ እየተከተላችኋቸው ትገኛላችሁና አሁኑኑ ወደከበረው ማንነታችሁ ተመለሱ። ካልሆነ ግን የኢትዮጵያ ዳግም ትንሣኤ ሲመጣ ለእናንተ የሞት ቀን ይሆንባችኋል።
:
➊➏ኛ).የዘንዶ ራስ ተቀጥቅጦ ልዩ ምግብ (ጤፍ) ከፈጣሪ የተሰጣቸው ሕዝቦች /ሐበሾች/ ያሉባት ምድር ነች ኢትዮጵያ።
:
አንተም የዘንዶውን ራስ ቀጠቀጥህ፣ ለኢትዮጵያዊያን ሰዎችም ልዩ ምግብን ሰጠሀቸው ይላል ቅዱስ መጽሀፍ። አስተውሉ! መርምሩም! የእኛ ምግብ አይጥ፣ እባብ፣ አህያ፣ ውሻ ወይም ሌላ የረከሰ ምግብ አይደለም። እንጀራ ነው እንጅ።
:
፪."ሐዲስ ኪዳን!"
:
➊ኛ).የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ በኮከብ እየተመሩ ሄደው የእጅ መንሻ /ገጸበረከት/ ካቀረቡለት (ሰብዐ ሰገል) መካከል የሀበሻው ንጉሥ ባዜን ይገኛል።
:
መድኃኒታችን ሲወለድ መወለዱን በኮኮብ የገለጸላቸው ለእስራኤላዊያን ወይም ለዐረቦች አይደለም። ለሐበሾች እንጅ። ይሄን ክብር ማን አገኘው?
:
➋ኛ).ማኅደረ መለኮት እመብርሃን ድንግል ማርያም በስደቷ ጊዜ በሰላም ያረፈችባትና በአስራትነት የተሰጠቻት እንዲሁም በተደጋጋሚ በልጇ መስቀል የባረከቻት ቅድስት ሀገር ቅድስት ምድር ኢትዮጵያ ነች።
:
ድንግል ሆይ የአስራት ሀገርሽን ኢትዮጵያን አስቢ! አሜን። ይህ ጸሎት ከየት የመጣ ይመስላችኋል? ዘልማዳዊ ነውን? አይደለም!
:
➌ኛ).ክርስትናን በጃንደረባዋ አማካኝነት ከዓለም ቀድማ የተቀበለችና መንግስታዊ ሐይማኖት እንዲሆን ያወጀች ሀገር ታላቋ ኢትዮጵያ ነች።
:
አስተውሉ! ከክርስቶስ ሐዋርያት የአንዱስንኳ ደም ሳይፈስባት በአራቱም ማዕዘናት የወንጌል ብርሀን የበራባት ቅድስት ሀገር ናት ኢትዮጵያ።
:
➍ኛ).ጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰቀልበትን መስቀል ተሸክሞ ወደ ራስ ቅል ሥፍራ /ቀራኒዮ/ ሲጓዝ መስቀሉን ተቀብሎ በመሸከም ኢየሱስን ያገዘው የቀሬናው ሰው ስምዖን ሐበሻ /ኢትዮጵያዊ/ ነው።
:
ሮማዊያን ለአይሁድ አሁዶች ደግሞ ለሮማዊያን አሳልፈው ሲሰጡት፣
:
ወታደሮቹና አለቆቻቸው ያለርኅራሔ ሲገርፉትና ሲያሰቃዩት፣
:
የእስራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ወዮ ወዮ እያሉ ሲያለቅሱለት፣
:
የለበሰውን ድርብ በፍታ አውልቀው እጣ ተጣጥለው ሲወስዱትና ከለሜዳ ሲያለብሱት፣
:
ሲያፌዙበትና ምራቅ ሲተፉበት፣ ሲገርፉትና ሲያዳፉት፣
:
የእሾህ አክሊል ሲያጠልቁለት፣

ሐበሻው የቀሬናው ሰው ስምዖን ግን አልጨከነበትም። ኢትዮጵያዊ ሩኅሩህና አዛኝ ነውና። ወዲያዉኑ መስቀሉን ተሸክሞ ነው ያገዘው። ጌታዬን መስቀሉን ተሸከመለት።

ዛሬ ግን መስቀሉን በአንገታችን እንኳን ልንሸከመው አንወድም። የክርስቶስን መስቀል ወርውረን ማተባችንን በጥሰን የውሻ ማሰሪያ ሀብል የብረት ሰንሰለት በአንገጣችን አጥልቀናል። በሰንሰለት የታሰርን (በምዕራባዊያን የሴራ ሰንሰለት የታሰርን) ውሾች መሆናችንን በአደባባይ እየመሰከርን ነው። ወዮልን!!!
:
➎ኛ).ይህ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል አንድም ነገር ሳይጎድለው ሙሉ መስቀሉ የሚገኘው ግሸን ደብረ ከርቤ /ኢትዮጵያ/ ውስጥ ነው።
:
አስተውሉ! ግሼን ማርያም የሚገኘው የመስቀሉ አንደኛው ክፍል ነው። አማናዊውን እውነተኛውን መስቀል ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ዓለም በተለይም የምስራቅ አብያተ ክርስትያናት ተከፋፍለውት ለግብጽ ደርሷት የነበረው የቀኙ ክፍል ነው።
:
➏ኛ).የአይሁድ ወታደሮች ጎኑን በወጉት ጊዜ እና በቸነከሩት ጊዜ የፈሰሰውን የክርስቶስን ደም መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በጽዋ ተቀብሎ ዓለምን ሁሉ ረጨ።
:
ይህ ክቡር ጽዋም ያለው ኢትዮጵያ /ሰሜን ሸዋ/ ውስጥ ነው። ይሄን ምስጢር ጸሀፊ ዓለምአየሁ ዋሴ እሸቴ “እመጓ” በተሰኘው መጽሐፉ ለመዳሰሥ ሞክሯል።
:
እውነት ነው። ያ በእለተ ሀሙስ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ደሙን የሰጠበትና ያ ቅዱስ ዑራኤል አማናዊውን የክርስቶስ ደም ዓለምን የረጨበት ቅዱስና ክቡር ጽዋ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
:
➐ኛ).በዓለም የመጀመሪያው የዜማ ደራሲ ቅዱስ ያሬድ ሐበሻ ነው።
:
እነቬትሆቭንና ሞዛርት ከመወለዳቸው ሽህ አመታት አስቀድሞ የነበረ፣ ዜማን በምልክት ያረቀቀ፣ የዜማ መጽሐፍትን የደረሰ፣ የግዕዝና ዕዝል የአራራይ ስልት ባለቤት ያሬድ ማኅሌታይ፣ ዘሩ ከሊቀ ካህኑ ከሙሴ ወንድም አሮን የሚመዘዘው ያሬድ ኢትዮጵያዊ ነው።
:
➑ኛ).ሦስቱንም ሕጎች ማለትም ሕገ ልቦና፣ ሕገ ኦሪትና ሕገ ወንጌልን የተቀበለች፣ ያስተናገደችና እያስተናገደች ያለች ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ናት።
Photo
Wait while more posts are being loaded