Profile cover photo
Profile photo
Addis Ababa Police Commission
1 follower
1 follower
About
Posts

Post has attachment
‹‹ ጥቀምት 06 ቀን 2010 ዓ/ም!! ››
‹‹ 10ኛው የሠንደቅ ዓላማ ቀን!! ›› በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተከብሯል፡፡ ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በኮሚሽኑ ቅጥር ግቢ ሠንደቅ ዓላማ ሰቅለዋል፡፡ የኮሚሽኑ አመራርና አባላት ለሠንደቅ ዓላማችን ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
PhotoPhotoPhotoPhoto
10/17/17
4 Photos - View album
Add a comment...

Post has attachment
አንድ ህዝብ አንድ አፍሪካ
Add a comment...

Post has attachment
‹‹ ራዕይ ሠንቀናል ለላቀ ድል ተነሳስተናል!! ››
‹‹ ራዕይ ሠንቀናል ለላቀ ድል ተነሳስተናል!! ›› በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 10ኛዉ ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀንን ለማክበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከ3መቶ በላይ በየደረጃዉ ከሚገኙ የፖሊስ አመራሮች ጋር ጥቅምት 2 ቀን 2010 ዓ.ም በኮሚሽኑ ሠላም አዳራሽ ዉይይት አደረገ፡፡
በውይይቱ ላይ ስለ በዓሉ አከባበር እንዲሁም ስለ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ታሪክ በዋናነት ተነስቶ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ተወያዮቹም ለሠንደቀ ዓላማ ክብር ሁሌም በፅናት እንቆማለን ሲሉ አሰተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡
PhotoPhotoPhoto
10/12/17
3 Photos - View album
Add a comment...

Post has attachment
የ2010 ዓ/ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ RUNING FOR A CAUSE በሚል መሪ ቃል ህዳር 17 ቀን 2010 ዓ/ም እንደሚካሄድ ዛሬ በሂልተን ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተነግሯል፡፡ ይህ በምክንያት እንሩጥ የተሰኘው የሩጫ ውድድር በበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ ለተሰማሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንደሚውል የተነገረ ሲሆን እስካሁን ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንደተለገሰም ጭምር ከመድረኩ ተነግሯል፡፡
Photo
Photo
10/12/17
2 Photos - View album
Add a comment...

መስከረም 30 ቀን 2010 ዓ/ም
የድምፃዊ ሀብተሚካኤል ደምሴ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ፡፡
የባህል ድምፃዊው ታህሳስ 21 ቀን 1944 ዓ/ም በቀድሞ አጠራር ወሎ ክ/ሀገር ለጋምቦ ደረባ የተወለደ ሲሆን በ1971 ዓ/ም በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተቀጠረ፤ በሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋችነትና በድምፃዊነት ጡረታ እስከወጣበት ጥር 01 ቀን 2004 ዓ/ም ድረስ ሲያገለግል ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በትያትር ትወና በክቡር ዶክተር ተስፋዬ አበበ የተደረሰውን ታጋይ ሲፋለም በ1971 ዓ.ም፣ በጌታቸው አብዲ የተደረሰውን መስተዋት፣ 1978 ዓ/ም በብሀኑ ዘሪሁን ባልቻ አባነፍሶ፣ ዱባና ቅል በአያልነህ ሙላት የተደረሰውን ቲያትር ተጫውቷል፡፡
ሀብተሚካኤል ደምሴ መስከረም 29 ቀን 2010 ዓ/ም በተወለደ በ66 ዓ/ም በደረሰበት ድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን መስከረም 29 ቀን 2010 ዓ/ም የሙያ አጋሮቹና አድናቂዎቹ በተገኙነበት በአስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ስርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንም ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ኮሚሽኑ የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል እያደረገ ላለው ጥረት ህብረተሰቡ ተገቢውን ተሳትፎና እገዛ እንዲያደርግ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
Add a comment...

Post has attachment
አርቲስ ኃብተሚካኤል ደምሴ
አርቲስ ኃብተሚካኤል ደምሴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ/ም ከቀኑ 4፡30 ሠዓት አካባቢ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አበበ ቢቂላ ስታዲየም መግቢያ አካባቢ ከዊንጌት ወደ ፒያሳ ሲጓዝ በነበረ ኮድ 3A 36102 አ/አ በሆነ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ተገጭቶ ህይወቱ አልፏል፡፡ የአደጋውን ምክንያት እያጣራ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
Add a comment...

Post has attachment
የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ለመላው የእምነቱ ተከታዩች በዓሉ የሰላም የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልፆል፡፡
በተባበሩት መንግስታት የትምህረት፤ ሳይንስና ባህል ድርጅት ዮኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገው በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ፣ የመንግስት በለስልጣናት የውጪ ሀገር ቱሪስቶች የሚታደሙበት የደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በዓሉ በጥሩ ሁኔታ እንዲከበር ኮሚሽኑ ከሌሎች የፀጥታ አካላት እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልፆል፡፡
በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን የደመራ ፕሮግራም ተጀምሮ አስከሚጠናቀቅ እና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፡-
 ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ወይም ኦሎፒያ
 ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ፤ ከቦሌ መድሃኒያለም ፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ
 ከሚክሲኮ አደባባይ በለገሃር ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት
 ከአራት ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሄራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ
 ከፖስታ ቤት ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ ሃራምቤ ሆቴል
 ከሳሪስ፣ በጎተራ ፣ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ መሾለኪያ
በአጠቃላይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚያገቡ መንገዶች ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ዝግ መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቆ
 ደንበል ሲቲ ሴንተር  ባንቢስ የገበያ አዳራሽ ኡራኤል ወደ ቦሌ እንዲሁም መገናኛ
 ደንበል ሲቲ ሴንተር  መስቀል ፍላወር ጎተራ
 ከካዛንቺስ ኡራኤል ታላቁ ቤተ-መንግስት ፍል ውሃ ሀራምቤ ሆቴል ብሄራዊ ቲያትር  ሜክሲኮ አደባባይ
 ከካሳንቺስ መናኸሪያ  ገብርኤል ማዞሪያ አራት ኪሎ እና ሌሎች መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች እነዚህን መንገዶች በአማራጭነት እንዲጠቀሙ እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትእዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
ከዚህ ቀደም የተከበሩ ሃይማኖታዊና ብሄራዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ወሳኝ ስራ ማከናወኑን ኮሚሽኑ አስታውሶ የዘንድሮው የደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ነዋሪው የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን ነፃ የስልክ መስመር 991 ወይም በ01- 11 -11- 01 11 ፣ 01 18- 33- 22- 21 እንዲሁም በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ነፃ የስልክ መስመር 816 ወይም 01- 15- 52- 63-03 ፣ 01- 15- 52- 63-03 መጠቀም የሚችል መሆኑን ተገልጻል፡፡
ለስራው ስኬታማነት ህብረተሰቡ እያደረገ ላለው ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋናውን እያቀረበ ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልፆል፡፡
PhotoPhotoPhoto
9/26/17
3 Photos - View album
Add a comment...

Post has attachment
Add a comment...

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት 57ቱ ተጠርጣሪዎች ከየትኞቹ ተቋማት እንደሆነ ይፋ አደረገ፡፡ ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በፅ/ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፡-
1. ከአዲስ አበባ ፅዳትና ውበት ዘላቂ ማረፊያ ኤጀንሲ፣
2. ከደራሽ ለመርካቶ ሸማቾች፣
3. ከጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር፣
4. ከአራዳ ክ/ከተማ ቤቶች ልማት፣
5. ከን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ቤቶችና ኮንስትራክሽን፣
6. ከአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ድርጅት፣
7. ከጉለሌ መሬታ ይዞታና ማስተላለፍ፣
8. ከአ/ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ጽ/ቤት፣
9. ከጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፅ/ቤት፣
10. ከአ/አበባ መገናኛ ብዙሀን ኤጀንሲ፣
11. ከአ/አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ማኔጅመንት፣
12. ከጉለሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ሲሆን ተጠርጣሪዎቹም በተሰረዘ ሰረሰኝ ክፍያ መፈፀም፣ የግንባታ ማቴሪያል ለግል ጥቅም ማዋል፣ የመንግስትን መሬት ለግለሰብ ማዋል፣ ጨረታ አሸናፊ ላልሆነ ድርጅት ስራን መስጠት፣ ለተሽከርካሪ የማያስፈልጉ ግዢዎችን መፈፀም፣ የልማት ተነሺ ላልሆኑ ሰዎች በተነሺዎች ስም የኮንደሚኒየም ቤት መስጠት ዋና ዋና ጥፋቶች ተብለው የተለዩ ሲሆን በወንጀሉ መንግስት ማግኘት ያለበትን ከ170 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅም አውለዋል ተብሏል፡፡ በግለሰቦች ስም ተዘጋጁ ካርታዎች፣ ሀሰተኛ ልዩ ልዩ ሰነዶችና ማህተሞች በኤግዚቢትነት መያዙንም ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ተናግረው ተጠርጠሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሰፊ ጊዜ የወሰደ የማስረጃ ማሰባሰብ ስራ የተከናወነ ሲሆን በፍ/ቤት ትዕዛዝ መሰረት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
Add a comment...

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የስራ ኃላፊዎችን፣ ሙያተኞችንና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በህዝብና በመንግስት የተጀመረውን የፀረ ሙስና ትግል በማስቀጠል በአ/አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ በተፈፀመ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው 57 (አምሳ ሀባት) በየደረጃው የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች፣ ሙያተኞችና ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡
በሙስና ወንጀሉ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉትም ከአ/አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር እና ከህዝብ በተገኘ መረጃ፣ ፖሊስ በስፋት ባከናወነው የማስረጃ ማሰባሰብና የምርመራ ስራ በሙስና ወንጀሉ በመጠርጠራቸው በፍ/ቤት የመያዣ ትዕዛዝ መሰረት እንደተያዙ በመግለጫው ጠቅሶ ምርመራው የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ህዝቡም ለፀረ ሙስና ትግሉ መሳካት እያደረገ ያለውን ድጋፍ ኮሚሽኑ አድንቆ በማናቸውም መንገድ መረጃ ማቅረብ እንደሚቻል አስታውቋል፡፡
Add a comment...
Wait while more posts are being loaded